ያለዕድሜ ጋብቻን ማቋረጥ በኢትዮጵያ

Publication

Authors
L Juanola

የ የስ አይ ዱ (YES I do) ፕሮግራም በአማራ ክልል በባህርዳር ዙሪያና በቀወት ወረዳዎች ባደረገው ጥናት የታቀዱ/ የተፈጸሙ ያለዕድሜ ጋብቻዎች እንደሚቋረጡ ለማወቅ ተችሏል፡፡ ይሁን እንጅ ያለእድሜ ጋብቻ በሚቋረጥበት ጊዜ በታዳጊ ልጃገረዶች ህይወት ላይ የሚያመጣውን ተፅዕኖ ለማወቅ የሚያስችል በጥናት የተደገፈ ውስን መረጃ ነው ያለው፡፡

ይህ አጭር ፖሊሲ ተኮር ጽሁፍ በ የስ አይ ዱ ፕሮግራም በተካሄደ ጥናት የተገኙትን የጥናቱን ዋና ዋና ጭብጦች የሚያሳይ ሲሆን ትኩረቱም ጋብቻቸው በተቋረጠባቸው ልጃገረዶች የህይወት ልምድ ዙሪያ ይሆናል፡፡ ፁሁፍ ፖሊሲ አውጭዎችና ፕሮግራም ተግባሪዎች ትኩረት ሊሰጧቸው የሚገባቸውን ዋና ዋና ነጥቦችን በመለየት ታዳጊ ልጃገረዶች ያለዕድሜ ጋብቻን ለማቋረጥ በሚያደርጉት ውጣውረድ የሚያስፈልጋቸውን ድጋፍ ከየትና እንዴት ያገኛሉ የሚለውን ለመጠቆም ታስቦ የተዘጋጀ ነው፡፡

The English version on this publication is available here